የ11ኛው አመት የ5,000 ሜትር ርቀት ሩጫ እና እርምጃ መርኃ ግብር ቅዳሜ ጁን 7, 2025 ይከናወናል!

የሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባላት እና ቤተሰቦቻቸው የሚሳተፉበት የ11ኛው አመት የ5,000 ሜትር ርቀት እርምጃ እና ሩጫ መርኅ ግብር ቅዳሜ ጁን 7, 2025 በሴንትፖል ከተማ በሚገኘው ኮሞ መናፈሻ ውስጥ (Como Regional Park) ከጠዋቱ 7 ኤ.ኤም. ጀምሮ ይከናወናል:

በውድድሩ ዕለት ለአሸናፊነት እንዲበቁ የእለት ከእለት የኑሮ እና ስራ ሁኔታዎ በሚፈቅደው መሰረት ቢያንስ በሳምንት 3 ቀናት እንቅስቃሴ በማድረግ የልምምድ ዝግጅትዎን በአፋጣኝ ይጀምሩ፤ ጀምረውም ከሆነ አጠናክረው ይቀጥሉበት።

የዚህን አመት ዝግጅት ለየት የሚያደርገው ወደአዲሱ ቤተክርስቲያናችን ከመዛወራችን በፊት ለመጨረሻ ጊዜ የምናደርገው መርኃግብር መሆኑ ነው:: ለዝግጅቱ እንቅስቃሴ እና ማስተባበር ጉዳይ የቤ.ክ. የጤና ክፍል: የስንበት ት/ቤት አባላት እና የስበካ ጉባኤው በመተባበር ለዝግጅቱ መሳካት ጥረት የሚያደርጉ ይሆናል:: ስለ መርኃግብሩ ዝርዝር በቅርቡ መግለጫዎችን እና ማስታዎሻዎችን እናወጣለን::

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የስበካ ጉባኤ

Mark the date!
Get ready to lace up your running or walking shoes! Our 11th year 5aK run and walk event will be held on Saturday June 7th, 2025 at 7am at Como Regional Park, St Paul, MN.

This is a fantastic opportunity to come together as a family and friends, stay active, and support our church congregation.

God willing, this will be our last 5K event before we transition to our new church building. So, start preparing to run or walk! Whether you decide to walk, jog or race, we would love to see you at the 5K event.

We will have more detailed info about the event soon. Stay tuned!

DSMA Sebeka Gubae!

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net