የቤዛ ኩሉ የስንበት ት/ቤት 28ተኛ ዓመት ክብረ በአል ዝግጅት ሂደት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

እንኳን ለዚህች ታላቅ እለት ለእለተ ሆሣዕና በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ::

ክርስቶስ የቤተክርስቲያን እራስ እንደሆነ ምእመናን ደግሞ የቤተክርስትያን አካል ናቸው::እንዲሁም ካህናት አባቶች ለቤተክርስትያን አገልግሎት ራስ እንደሆኑ ሰንበት ትምህርት ቤት ደግሞ ለቤተክርስትያን አገልግሎት አካላቶች ነን::

እኛ የደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን የቤዛ ኲሉ ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ሰንበት ት/ቤታችን የተመሰረተበትን 28ተኛ ዓመቱን ከበአለ ትንሳኤ በኃላ በታላቅ ድምቀት ለማክበር ዝግጅቶችን እያዘጋጀን እንገኛለን::

ስለሆነም በየአመቱ እንደተለመደው የሰንበት ት/ቤታችንን ለማጠናከርና አገልግሎታችንን ለማሳደግ ይረዳን ዘንድ ከወዲሁ ገቢ ማስገኛ የሚሆኑ :-

  • የተለያዩ ስጦታ ያላቸው የዕጣ ትኬቶች (የመሸጫ ዋጋ $10)
  • ቲሸርቶች (የመሸጫ ዋጋ $15)
  • ከ8 ዓመት በታች ላሉ ልጆች ነጠላ (የመሸጫ ዋጋ $25)
  • ለአዋቂዎች የሚሆኑ ነጠላዎች (የመሸጫ ዋጋ $35)

አዘጋጅተን በጎግል ፎርም በቤተክርስትያኑ ለአገልግሎት በምንጠቀምባቸው ዌብሳይት ላይ በቫይበርና በዋትሳፕ እንዲሁም በቴሌግራም ግሩፕ ላይ አስቀምጠናል። ሁላችሁም ለዚህ አገልግሎት መሳካት የምትችሉትን ለሽያጭ ያቀረብናቸዉን በመግዛት ትተባበሩን ዘንድ በሰንበት ት/ቤታችን ስም ጥያቄአችንን እናቀርባለን::

እግዚአብሔር አምላክ ለዚህች ዕለት በሰላም በጤና ጠብቆ እንዳደረሰን ሁሉ ለበዓለ ትንሳኤው ከቁጥር ሳያጎድል በሰላም ያድርሰን::ከሁሉ በላይ ደግሞ በሰማያዊት እየሩሳሌም ሰብስቦ እንድናመሰግነው እርሱ ይፍቀድልን።

ወስበሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!

ጎግል ፎርም ማዘዢያ ፎርም ሊንክ