በኢትዮጵያ አቆጣጠር የ2015 ዓ.ም.ን መገባደጃ በመንተራስ በቀሪዎቹ የነሐሴና ጳጉሜ ወሮች የአዲስ የቤተክርስቲያን አባላት የትውውቅ ጊዜ እና የነባር የቤተክርስቲያን አባላት እንቅስቃሴ መርኅግብሮች እንዲታቀዱ የአስተዳደር ቦርዱ ወስኖ የሚከተሉት መርኅግብሮች እንዲከናወኑ ይሆናል:: አዲስ የቤተክርስቲያን አባል ማለት በኢትዮጵያ አቆጣጠር የ2015 ዓ.ም የደብራችን አባል የሆኑ ማለት ነው::
የአዲስ አባላት የትውውቅ መርኅግብር:-
- እሁድ እሁድ ከቅዳሴ አገልሎት ፍፃሜ በሗላ እታች አዳራሽ ውስጥ አዲስ የቤተክርስቲያን አባሎቻችንን የእንኳን የደብራችን አባል ሆናችሁ በማለት የካህናት ፣ የአስተዳደር ቦርድ እና የአባላት ማኅበራት ተወካዮች ጋር ትዉዉቅ ይደረጋል::
- የእዲስ አባላት ስም ዝርርዝም እታች አዳራሽ ውስጥ በሚገኘው ቴሌቪዥን ስኪሪን ላይ ይተላለፋል::
- የቤተክርስቲያን አባልነት መታወቂያ ካርድ ላልወስዱ በእለቱ የቤተክርስቲያን አባልነት መታወቂያ ካርድ እንዲያወጡ ይደረጋል::
- በእለቱም ለ አ ዲስ አባላት ቡና ፣ ሻይና ዳቦ ካለ ይቀርባል::
የነባር የደብራችን አባላት እንቅስቃሴ መርኅግብር:-
- ነባር የቤተክርስቲያን አባሎች እሁድ እሁድ አታች አዳራሽ ውስጥ በሚገኘው የቦርድ አባላት የጠረጴዛ ቢሮ ድረስ በመሄድ የአባላት መዝገብ ላይ ያለው አድራሻችሁ ስልክ ቁጥራችሁና ኢሜል ትክክል እንደሆነ እንድታረጋግጡልን በአክብሮት እንጠይቃለን::
- የደብራችን አባልነት አዲስ መታወቂያ ካርድ ያላወጡ በእለቱ የቤተክርስቲያን አባልነት መታወቂያ ካርድ እንዲያወጡ ይደረጋል::
- የየደብራችን አባልነት የወርሀዊ መዋጮአችሁ መጠናቀቁን የቦርድ አባላትን መጠየቅና ውዝፍ ካለ በወቅቱ እንዲጠናቀቅ መሞከር
- የደብራችን አባል ያልህኑ ዘመዶች ፣ ጏደኞች እና ወዳጆችን የቤተክርስቲያኗ አባል እንዲሆኑ ማነቃቃትና ማበረታታት
- የቤተክርስቲያናችን የመረዳጃ ማህበር አባል ለመሆን መሞከር
- ገቢው ለአዲስ ቤ.ክ. ማስሪያ የሚውል የበጎፍቃድ ስራ አገልግሎት ላይ ለመሳተፍ ከፕሮግራሙ እስተባባሪ ከዶ/ር አሻግሬ መረጃ መጠየቅ
መርኅግብሮቹ ከመጪው እሁድ የቅዳሴ አገልሎት ፍፃሜ በሗላ ለአምስት ተከታታይ እሁዶች የምንከታተላቸው ይሆናል:: ቀኖቹም ነሐሴ7(Sug 13), ነሐሴ14(Aug 20), ነሐሴ21(Aug 27), ነሐሴ28(Sep 3), ጳጉሜ5(Sep 10) ናቸው::
ያቀድናቸውና ያሰብናቸው እንዲሳኩ ውድ የደብራችን ነባርና አዲስ የቤተክርስቲያን አባላት ከምንጊዜውም በበለጠ ሁኔታ የሰበካ ጉባዔውን እንድትተባበሩት በትህትና እንጠይቃለን:: በፅሁፍም ሆነ የመረጡትን የሰበካ ጉባዔ አባል በግል በመቅረብ አዳዲስ የአሰራር ሃሳቦችን እንድታካፍሉን ይሁን::