Category Archives: events

ለአመታዊው የደብረስላም የጤና ቀን June 7, 2025 ይቀላቀሉን

ማስታወቂያ

እኛ የደብረሰላም መድኀኔዓለም ቤ.ክ. የጤና ክፍል ከስንበት ት/ቤት እና ከስበካ ጉባኤው ጋር በመተባበር አመታዊ የጤና ቀን መርኅግብርን (5K Run &Walk) በታላቅ ድምቀት ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆናችንን ስንገልጽላችሁ እጅግ በጣም ደስ እያለን ነው። እርስዎም በተለያዩ የአካል እንቅስቃሴዋች እና መዝናኛዎች ላይ በመሳተፍ  አብራችሁን ስትዝናኑ እድትውሉ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

  • ቀኑ  – ቅዳሜ June 7,2025
  • ሰዓቱ –  ከ7 am ጀምሮ
  • አድራሻው : Como Regional Park

በቀኑ ከሚኖሩን ክንውኖች መካከል

  • የጤና ምርመራዋች 
  • የ5ሺ ሜትር ርቀት እርምጃ እና ሩጫ
  • የተለያዩ ውድድሮች: ጨዋታዎች እና የአካል እንቅስቃሴዋች
  • ለሽያጭ የሚቀርቡ ምግቦች እና መጠጦች ጥቂቶቹ ናቸው።

ይህንን ቀን ከወዳጅ ዘመዶቾ እና ከመላው ቤተሰቦቾ ጋር ተዝናንተው እና ተደስተው የሚውሉበት ቀን እንደሚሆን እያረጋገጥን ይሄ ከወዲሁ እንዲዘጋጁ በማክበር እናስታውቃለን::

በእለቱ በሚኖሩት ፕሮግራሞች ለመሳተፍ የምትችሉበትን የመመዝገቢያ ፎርም እና የቲኬት ሽያጭ በቅርቡ እንጀምራለን::

የደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤ.ክ. የጤና ክፍል

Join Us for the Annual DSMA Health Day on June 7, 2025!

We’re excited to announce the annual Health Day at Debreselam Medhanealem Ethiopian Orthodox Church! This is an annual event being organized by our own parish health group. Join us for a day dedicated to wellness, fitness, social and fun.

  • Date:  Saturday June 7, 2025
  • Time: From 7 am
  • Location: Como Regional Park, St. Paul

Enjoy a variety of activities, including:

  • Free health screenings
  • 5K run and walk
  • Various other games
  • Food and beverages

Don’t miss this opportunity to focus on your well-being and connect with fellow families in faith! We look forward to seeing you there!

We will soon post information regarding event registration and ticket sales. Stay tuned!

DSMA Parish Health Group

የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ እሁድ ሜይ 11, 2025 ይደረጋል!

የደብራችን አባላት ጠቅላላ ጉባኤ እሁድ ሜይ 11, 2025 ከቅዳሴ አገልግሎት በሁዋላ የሚደረግ መሆኑን በማክበር እንገልፃለን:: በዚሁም እለት የቤተክርስቲያናችን አባላት በሙሉ በስብስባው ላይ እንድትገኙ በታላቅ  ትህትና  ጥሪያችንን  እያቀረብን በስብስባውም ላይ ለመሳተፍ የአባልነት ወርሀዊ ክፍያችንን ሙሉ ለሙሉ መክፈል እንደሚጠበቅብንም በማክበር  እናሳስባለን::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Your attendance at the next general assembly is kindly requested on Sunday May 11, 2025, immediately following the Sunday church service. To attend the general assembly, church members must be up to date with their monthly membership dues. We look forward to your active participation as we come together in faith and unity.

Blessings.

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የስበካ ጉባኤ

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net

የቅዱስ ገብርኤልን የዋዜማ አገልግሎት እና በዓለ ንግስ በደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ያድርጉ!

በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የዘንድሮዉን ዓመት የቅዱስ ገብርኤል የዋዜማ አገልግሎት ቅዳሜ ታኅሳስ 19, 2017 ከቀኑ 4:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ (Saturday Dec 28, 2024 from 4:00 pm) ፣ ቀጥሎም እሁድ ታኅሳስ 20, 2017 ከ2:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ (Sunday Dec 29, 2024 from 2:00 am) በማህሌት የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ በደመቀ ሁኔታ ታከብራለች:: በእለቱም ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታቀርባለች::

መቼ? / When?
የዋዜማ አገልግሎት፣ ቅዳሜ ታኅሳስ 19, 2017 ከቀኑ 4:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ (Saturday Dec 28, 2024 from 4:00 pm)
በዓለ ንግስ ፣ እሁድ ታኅሳስ 20, 2017 ከ2:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ (Sunday Dec 29, 2024 from 2:00 am) በማህሌት

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net

በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢ.ኦ.ተ. ቤተክርስቲያን በ2017 ዓ.ም. የሚከበሩ በዓላት እና የአጿማት ቀን መቁጠሪያ

የ2017 ዓ.ም. ከገባ የመጀመሪያዎቹን ሁለት ወሮች አገባድደናል:: አዲስ አመት እንደመሆኑም የአመታዊ፣ የንግሥ በዓላት እና የአጿማት ቀን አቆጣጠሩ ላይ ብዙ ማወቅ የምትፈልጉት እንዳሉ እንገነዘባለን:: ለምሳሌም ያህል የጾም ቀኖች እና ወራቶች የትኞቹ ናቸዉ? የአመታዊ እና የንግሥ በዓላት የሚዉሉባቸዉ ቀኖችስ የትኞቹ ናቸዉ? በዩኤስ ባንክ ስታዲየም ለአዲስ ቤተክርስቲያን ማሰሪያ የሚውል የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ቀኖች እና ወራቶችስ የትኞቹ ናቸዉ? የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የህጻናት ታዳጊዎችና ወጣቶች አገልግሎት መርኃ ግብሮች መቼ መቼ ሊውሉ እንደሚችሉ እቅድ እና ፕሮግራም ወጥቶላቸዋል ወይ?

ይህ የቀን መቁጠሪያ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልሰ ይሰጣል:: ስለሆነም ከወዲሁ በመዘጋጀት ከመላዉ ቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተካፊይ እንዲሆኑ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

  • ማሕሌተ ጽጌ / ወርሃ ጽጌ (የፍቃድ ጾም ነው):- ከመስከረም 26, 2017 እሰከ ህዳር 6, 2017 (Oct 6, – Nov 15, 2024)
  • ጥቅምት መድኃኔዓለም :- በዓለ ንግስ ጥቅምት 24, 2017 ( Nov 3, 2024)
  • ኅዳር ሚካኤል :- በዓለ ንግስ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ቀን :ህዳር 15, 2017 (Nov. 24, 2024) / Hidar St. Michael
  • ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) :- ከህዳር 15,2017 አስከ ታህሳስ 28, 2017 (Nov 24, 2024 – Jan 7, 2025)
  • የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- እሑድ, ኅዳር 22, 2017 (Dec 1, 2024) / U.S. Bank Stadium volunteer work
  • የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- እሑድ, ኅዳር 29, 2017 (Dec 8, 2024) / U.S. Bank Stadium volunteer work
  • የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- ሰኞ, ታህሣሥ 7, 2017 (Dec 16, 2024) / U.S. Bank Stadium volunteer work
  • የታኅሳስ ገብርኤል :- በዓለ ንግስ – ታኅሳስ 20, 2017 (Dec. 29, 2024) / Tahisas St. Gabriel
  • የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- እሑድ, ታህሣሥ 20, 2017 (Dec 29, 2024) / U.S. Bank Stadium volunteer work
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የልጆች የገና በዓል ዝግጅት መርኃ ግብር:- ቅዳሜ, ታህሣሥ 26, 2017 (Saturday Jan 4, 2025)
  • የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት (ገና) :- ታኅሳስ 29, 2017 (Jan 7, 2025) / The Birth of Christ
  • የጥምቀት ጾም (ጾመ ጋድ) :- ጥር 10, 2017 (Jan 18, 2025)
  • ከተራ :- ጥር 11, 2017 (Jan 19, 2025)
  • ቃና ዘገሊላ:- ጥር 12, 2017 (Jan 20, 2025) / The Baptism of Christ (Epiphany).
  • ጾመ ነነዌ :- የካቲት 3, 2017 (Feb 10, 2025)
  • የየካቲት ኪዳነምሕረት :- በዓለ ንግስ – የካቲት 16, 2017 (Feb. 23, 2025) / The Covenant of Virgin Mary.
  • የዓብይ ጾም (ጾመ ሁዳዴ ) :- የካቲት 17,2017 አስከ ሚያዝያ 12, 2017 (Feb 24, 2025 – April 20, 2025)
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የበገና ምሽት:- ቅዳሜ, መጋቢት 6, 2017 (Saturday, March 15, 2025)
  • ደብረ ዘይት:- መጋቢት 14, 20117 (March 23, 2025) / Debrezeit
  • የመጋቢት መድኃኔዓለም በዓለ ንግስ :- መጋቢት 28, 2017 (April 6, 2025) / Megabit Medhanealem
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የሆሳዕና መርኃ ግብር:- ቅዳሜ, ሚያዝያ 4, 2017 (Saturday, April 12, 2025)
  • ሆሳዕና :- ሚያዝያ 5, 2017 (April 13, 2025) / Hosanna
  • ሰሙነ ሕማማት :- ከሚያዝያ 6, 2017 እስከ ሚያዝያ 11, 2017 (April 14 – 19, 2025) / Holy/Passion week.
  • ጸሎተ ሐሙስ :- ሚያዝያ 9, 2017 (April 17, 2025) / Maundy Thursday
  • ስቅለት :- ሚያዝያ 10, 2017 (April 18, 2025) / Good Friday (Crucifixion)
  • ቅዳሜ ስዑር (ሚያዝያ 11, 2017):- የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የልጆች ትምህርት የለም / Sunday school closed on Saturday April 19, 2025.
  • ትንሣኤ :- ሚያዝያ 12, 2017 (April 20, 2025) / Easter
  • የእመቤታችን ልደት በአል :- ግንቦትt 1, 2017 (May 9, 2025) / The Birthday of Virgin Mary
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የልጆች ትምህርት የማጠቃለያ ፈተና እለት:- ቅዳሜ, ግንቦት 16, 2017 (May 24, 2025)
  • እርገት :- ግንቦት 21, 2017 (May 29, 2025) / Ascension. The day of Holy Spirit
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የልጆች ትምህርት መጨረሻ እለት:- ቅዳሜ, ግንቦት 23, 2017 (May 31, 2025)
  • ጰራቅሊጦስ:- ሰኔ 1, 2017 (June 11, 2025) / Peraklitos
  • ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) :- ከሰኔ 2, 2017 እሰከ ሀምሌ 5, 2017 (June 9, 2025 – July 12, 2025)
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት ለህጻናት ታዳጊዎችና ወጣቶች የሰመር ኮርስ :- ከሰኞ, ሰኔ 2, 2017 እሰከ ሰኞ, ሰኔ 9, 2017 (June 9, 2025 – June 16,2024) / Kids summer course
  • ጾመ ድህነት :- ሰኔ 11, 2017 (June 11, 2025)
  • ሰኔ ሚካኤል :- ሰኔ 15, 2017 (June 19) Sene St. Michael.
  • የቤዛ ኩሉ የስንበት ት/ቤት 28ተኛ ዓመት ክብረ በአል ዝግጅት መርኅ ግብር:- ከሰኞ, ሰኔ 16, 2017 እሰከ ዓርብ, ሰኔ 20, 2017 (June 23, 2025 – June 27, 2025) / Beza Kulu Sunday School Annual Celebration
  • በአለ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ( አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ):- ሐምሌ 5, 2017 (July 12, 2025) / The Martyrdom of Peter and Pau
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የልጆች ሰመር ካምፕ :- ከሰኞ, ሐምሌ 7, 2017 እስከ ዓርብ, ሐምሌ 11, 2017 (Monday July 14, 2024 – July 18, 2024) / kids summer camp
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የታዳጊና የወጣቶች የመዝናኛ እና የሽርሽር ጉዞ ለ21ኛ ጊዜ:- ሓሙስ, ሐምሌ 17, 2017 (Thursday July 24,2025) / Field Trip for children under 12 years old
  • የሐምሌ ገብርኤል :- ሐምሌ 20, 2017 (July 27, 2025) / Hamle St. Gabriel.
  • 11ኛዉ የ5000 ሜትር ርቀት ሩጫና እርምጃ መርኃ ግብር:- ቅዳሜ, ሐምሌ 26, 2017 (Saturday, August 2, 2025) / 11th annual 5K run and walk
  • ጾመ ፍልሰታ :- ከነሀሴ 1, 2017 – ነሀሴ 16, 2017 (August 7 – 22, 2025)
  • የቤዛ ኵሉ ስንበት ት/ቤት የልጆች ደብረ ታቦር በዓል ዝግጅት:- ነሐሴ 10, 2017 (August 16, 2025)
  • ደብረ ታቦር :- ነሐሴ 13, 2017 (August 19, 2025) / Transfiguration (Debre Tabor)
  • ነሐሴ ኪዳነምሕረት :- ነሐሴ 16, 2017 (August 22, 2025) / The assumption of Virgin Mary.

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406, U.S.A.
ስልክ: +1(612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!

ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለማዳረስ ያለ ማቋረጥ አገልግሎት እየሰጠች ትገኛለች። ይህንን ተልእኮዋን ከግብ ለማድረስ እኛ ልጀቿም ፍጹም መንፈሳዊ በሆነ ትጋት ከጎኗ በመሆን ልናገለግል ይገባል። የሰው ልጅ አንዱ የተፈጠረበት ዓላማም አገልግሎት በመሆኑ ጊዜን፣ ገንዘብን፣ ጉልበትን እና ዕውቀትን ለእግዚአብሔር ለመስጠት ፈጽሞ ቸል ልንል አይገባንም። ለዚህም ነው በመጽሐፍ “ ታገለግሉት ዘንድ መርጧችኋል እና ቸል አትበሉ::” (መዋ.ዜና.፳፱፥፲፩) ተብሎ የተጻፈልን። ዛሬም እዚህ የተሰበሰብንበት አላማ ይኸው ነውና የረዳን አምላካችን ክብር ምስጋና ይግባው።

የነገዋን ቤተ ክርስቲያን የተሻለችና ለትውልዱ እስከ ሙሉ ክብሯ እንድትተላለፍ ቅድሚያ ሰጥተን መሥራት ካሉብን በርካታ ጉዳዮች አንዱ በቂ እና ምቹ አብያተ ክርስቲያናትን በተለያዩ አካባቢዎች ማስፋፋት እንደመሆኑ መጠን በሚኒሶታ የምንሰራው ህንጻ ቤተክርስቲያን እንደአብነት የሚጠቀስ ይሆናል።

የዚህንም አመት መስቀል በዓልን ስናከብር እግዚአብሔር በስደት አገር አብዝቶን ቤቱን ለመስራት ከቋፍ ላይ በመሆናችን በታላቅ ደስታ እና የምስጋና መንፈስ ነው። ጳጉሜን 2, 2016 (September 7, 2024) ብጹዕ አባታችን አቡነ ቴዎፍሎስ የካሊፎርንያና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት ለአዲሱ ሕንጻ ግንባት የቁፋሮ ጅማሬ ስነስርዓት በተካሄደበት ወቅት ከሁለት መቶ ሺህ ዶላር በላይ ተሰባስቧል። የግንባታ ሂደቱን ለመስጀመር የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ማለትም ንድፍ ስራ መጠናቀቅ፤ ከህንጻ ተቋራጭ ጋር ስምምነት ማካሄድ እንዲሁም ከከተማ ምክር ቤት ፈቃድ ማግኘትን የመሳሰሉ ጉዳዮች የተሟሉ ሲሆን የግንባታ ሂደቱም እግዚአብሔር ቢፈቅድ በጥቅምት ወር (October 2024) ተጀምሮ በሚቅጥለው አመት ሐምሌ (July 2025) ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህ አጋጣሚ የሚኒሶታ እና አካባቢው ምዕመናን የዚህ ታላቅ አላማ አካል በመሆን ከበረከቱ እንድትሳተፉ ጥሪያችንን እናስተላለፋለን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቅርቡ ስራው የሚጀመረው ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ህንጻ ንድፍ

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406, U.S.A.
ስልክ: +1(612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የታዳጊና የወጣቶች የመዝናኛ እና የሽርሽር ጉዞ ለ20ኛ ጊዜ JULY 29, 2024 ተደረገ::

በደብራችን በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን በየዓመቱ በአመት አንድ ጊዜ የሚደረገውን የታዳጊና የወጣቶች መዝናኛ መርኃ ግብርን ሙሉ ወጪ ዶክተር ሲራቅ ኃይሉ በመሸፈን ሰኞ JULY 29, 2024 ልጆቻችን ወደ ባንከር ቢች በመሄድ ተዝናንተዋል::

በዚህ አጋጣሚ ዶ/ር ሲራክን እግዚአብሔር አምላክ በረከቱን ይስጥልን እያልን በመልካም ሥራቸው ሁሌም ከጎናችን ስለሚሆኑ እናመሰግናቸዋለን።

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406, U.S.A.
ስልክ: +1(612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

የአስረኛው አመት የ5,000 ሜትር ርቀት ሩጫ እና እርምጃ መርኃ ግብር በመጪው ቅዳሜ ጁን 15, 2024 ይከናወናል!

የሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባላት እና ቤተሰቦቻቸው የሚሳተፉበት የአስረኛው አመት የ5,000 ሜትር ርቀት ሩጫ እና እርምጃ መርኃ ግብር በመጪው ቅዳሜ ጁን 15, 2024 (ቅዳሜ ሰኔ 8, 2016) በሴንትፖል ከተማ በሚገኘው ፌለን መናፈሻ ውስጥ (1600 Phalen dr, St. Paul, MN 55106) ከጧቱ 8 ኤኤም ጀምሮ ይከናወናል::

ለዚሁም እለት የሚሆን የተሳትፎ መግቢያ ቲኬት ተዘጋጅቶ ቀርቧል:: ቲኬቱን በየአላችሁበት ቦታ ሆናችሁ በሚመቻችሁ ጊዜ ስአት በኦንላይን መንገድ ለመግዛት ትችላላችሁ::

ቲኬቱን በኦንላይን ለመግዛት ይህን ይጫኑ

የሚቀጥለውን ምስል በስልካችሁ ካሜራ ፎቶግራፍ ለማንሳት ስትሞክሩ በቀጥታ ቤተክርስቲያናችን ባዘጋጀችው የኦንላይን ገንዘብ መክፈያ ቦታ ይመራችኇል::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406, U.S.A.
ስልክ: +1(612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ አደረሳችሁ!

ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም
እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ (መዝሙረ ዳዊት ፸፰ ቁጥር ፷፭)

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤

ቅዳሜ ሚያዝያ 26, 2016 ዓ.ም. (Saturday May 4, 2024) ከ 5 ፒ.ኤም. ጀምሮ የትንሳኤን በአል በደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በመገኘት በማህሌት እና በቅዳሴ እብረን እናክብር!

የመድኃኔዓለም ቤተሰቦች ፣ ከዚህ በላይ ፎቶው የሚታየው የቤተክርስቲያናችን ተተኪ መምህር ዲያቆን ቃለ አብ አብይ ነዉ::

ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታቀርባለች::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

የሆሳዕና በዓልን እና የሰሙነ ሕማማት መርኃ ግብርን በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አብረን እናክብር!

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤

የሆሳዕና በአል

ማህሌት እሁድ ሚያዝያ 20, 2016 ከ 3 ኤ.ኤም. ጀምሮ (Sunday, April 28, 2024, from 3 am)

የሰሙነ ሕማማት መርኃ ግብር / Holy/Passion week.

ከስኞ ሚያዝያ 21, 2016 እስከ እስከ ረቡዕ ሚያዝያ 23, 2016, በየቀኑ ከ 6 ኤ.ኤም እስከ 2 ፒ .ኤም (Monday Apr 29, 2024 – May 1, 2024, 6 am – 2pm daily)

ጸሎተ ሐሙስ :- ሀሙስ ሚያዝያ 24, 2016 ከ 5 ኤ.ኤም. እስከ 2 ፒ.ኤም. (Thursday May 2, 2024, 5am – 2pm ) / Maundy Thursday

ስቅለት :- አርብ ሚያዝያ 25, 2016 ከ 6 ኤ.ኤም እስከ 6 ፒ.ኤም 6am – 6pm (Friday May 3, 2024) / Good Friday (Crucifixion)

ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታቀርባለች::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

እንዳያመልጣችሁ! የበገና ምሽት ቅዳሜ ኤፕሪል 13, 2024 በሚኒስታ ደብረስላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አዳራሽ

ታላቅ የበገና ምሽት

በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ታዳጊ እና ወጣቶችተዘጋጅቶ ይቀርባል::

መቼ : ሚያዝያ 5, 2016 ዓ.ም. (April 13, 2024) ከቀኑ 4:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ

እንዳያመልጣችሁ!
አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

በአብይ ጾም ውስጥ ያሉ ሳምንታት ስያሜ

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤
እንኳን ለ2016 ዐብይ ጾም አደረሰን!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለጾም ሥርዓት እና ደንብ አውጥታ በዓመት ውስጥ ሰባት የአዋጅ አጽዋማት እንዳሉና ማንኛውም ክርስቲያን እነኝህን አጽዋማት እንዲጾሙ ታዛለች። ከነዚህም አንዱ እና ታላቁ ጾም ዛሬ ሰኞ መጋቢት 2/2016 (March 11, 2024) የጀመርነው የአብይ ጾም ነው:: ለዚህም ቤተክርስቲያናችን እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቷን ትገልጻለች።

ዐቢይ ጾም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ የጾመው ጾም እና ለእኛ አራያ የሆነበት ጾም ነው። እኛም እንድንጾማቸው በቤተ ክርስቲያናችን ከታዘዝናቸው ሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ ነው። እኛ ምእመናን ጌታችን ያደረገውን ምሳሌ ተከትለን ጾሙን በየዓመቱ እንጾመዋለን። ዐቢይ ጾም ስምንት ሳምንታት (፶፭ ቀኖች) ሲኖሩት በውስጡ ስምንት ቅዳሜዎች፣ ሰባት እሑዶች ይገኛሉ።እነዚህም ዐሥራ አምስት ቀናት ሲሆኑ በእነዚህ ቀናት ከጥሉላት እንጂ ከእህል ውኃ ስለማይጦሙ እነዚህ ቀናት ሲቀነሱ የጦሙ ወራት ዐርባ ቀን ብቻ ይሆናል።

ዓብይ ጾም የተባለበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ስለሆነና ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎችን ድል የተነሱበት በመሆኑ ዛሬም ክርስቲያኖች የአምላካችንን አርአያ ተከትለን ሰይጣንን ድል የምንነሳበት ጾም ስለሆነ ነው።

የዐብይ ጾም በተለያዩ ስሞችም ይጠራል

  • ሁዳዴ ጾም ይባላል። ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት ሥፍራ ሁዳድ ይባላል። በመሆኑም ዐቢይ ጾምም ከአጽዋማት ሁሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ክርስቲያኖች የሆኑ ምዕመናን ሁሉ ስለሚጾሙት የሁዳዴ ጾም ተባለ።
  • ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ፵ ቀን ስለሆነ ጾመ ዐርባ ም ይባላል /ማቴ.፬፥፩/

በአብይ ጾም ውስጥ ያሉ ሳምንታት ስያሜ

  • ዘወረደ
  • ቅድስት
  • ምኵራብ
  • መጻጕዕ
  • ደብረዘይት
  • ገብርኄር
  • ኒቆዲሞስ
  • ሆሳዕና
  • ትንሳኤ ናቸው ::

የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በአብይ ጾም ያላት የአገልግሎት መርኃ ግብር

  • ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 6 ኤ.ኤም እስከ 10 ኤ.ኤም የኪዳን ፀሎት አገልግሎት ይሰጣል።
  • ዘወትር ቅዳሜ ከጠዋቱ 6 ኤ.ኤም እስከ 8 ኤ.ኤም የኪዳን ፀሎት ይደርሳል።
  • ዘወትር እሁድ ከንጋቱ 3 ኤ.ኤም ጀምሮ የፀሎት፣ የክርስትና፣ የቅዳሴ አገልግሎቶች ይሰጣል::

ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተካፊይ እንዲሆኑ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአገልግሎት ቀን መቁጠሪያ ::

  • የዓብይ ጾም (የሁዳዴ ጾም) :- ከመጋቢት 2 አስከ ሚያዝያ 27 (Monday March 11, 2024 – Sunday May 5, 2024)
  • መጋቢት መድሐኔዓለም :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : መጋቢት 29, 2016 (Sunday Apr. 7, 2024) / Megabit Medhanealem / The original Crucifixion.
  • ደብረ ዘይት :- መጋቢት 29, 2016 (Sunday April 7, 2024) / Debrezeit
  • ሀሳዕና :- ሚያዝያ 20, 2016 (Sunday April 28, 2024) / Hosanna
  • ሰሙነ ሕማማት :- ሚያዝያ 21, 2016 እስከ ሚያዝያ 26, 2016 (Monday April 29, 2024 to Friday May 3, 2024) / Holy/Passion week.
  • ጸሎተ ሐሙስ :- ሚያዝያ 25, 2016 (Thursday May 2, 2024) / Maundy Thursday
  • ስቅለት :- ሚያዝያ 26, 2016 (Friday May 3, 2024) / Good Friday (Crucifixion)
  • ትንሣኤ :- ሚያዝያ 27, 2016 (Sunday May 5, 2024) / Easter Sunday

በዚህ አብይ ጾም ሁላችም ስለሀገራችን እና ስለ ቅድስት ቤተክርስትያናችን አብዝተን የምንጸልይበት እኛም በረከት የምናገኝበት በስጋ ወደሙ የምንከብርበት ያድርግልን::

ጽሁፉን ያዘጋጀችው ወይዘሮ ሐና ስዩም ነች::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

የየካቲት ኪዳነምሕረትን የዋዜማ አገልግሎት እና በዓለ ንግስ በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያክብሩ!

በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እንኳን ለየካቲት ኪዳነምሕረት በዓለ ንግስ በስላም አደረሳችሁ እያለች፣ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 16, 2016 ከቀኑ 4:00ፒ.ኤም. ጀምሮ (Saturday Feb. 24, 2024 from 4:00 pm) በዋዜማ፣ ቀጥሎም እሁድ የካቲት 17, 2016 ከ2:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ (Sunday Feb. 25, 2024 from 2:00 am) በማህሌት የየካቲት ኪዳነምሕረትን በዓለ ንግስ በደመቀ ሁኔታ ታከብራለች:: በእለቱም ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታቀርባለች::

መቼ? / When?
የዋዜማ አገልግሎት፣
ቅዳሜ የካቲት 16, 2016 ከ4:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ (Saturday Feb. 24, 2024 from 4:00 pm)
በዓለ ንግስ
እሁድ የካቲት 17, 2016 ከ2:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ (Sunday Feb. 25, 2024 from 2:00 am)

ፎቶግራፉ የሚያሳየዉ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የቤዛ ኩሉ የሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶች በዚህ አመት የጥምቀት በአል አከባበር መርኃግብር ላይ ነዉ::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net

በፌስቡክ እንዲከተሉን ይህን ይጫኑ

Click Here to Follow Us On Facebook

የዘንድሮው የከተራ እና ጥምቀት በዓል አከባበር እና የሃያ ሰባት አመቱ ቤዛኩሉ

በዚህ አመት የከተራ እና ጥምቀት በዓላት  ቅዳሜ ጥር 11, 2016 (Saturday Jan 20, 2016) እና እሁድ ጥር 12, 2016 (Sunday Jan 21, 2016) Bloomington Road, Fort Snelling, St. Paul, MN 55111 በሚገኘው ቦታ እንደወትሮው በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል:: የዘንድሮውን የጥምቀት በአል አከባበር ደማቅ እና ልዩ ያደረገው ነገር ቢኖር የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ለመጀመሪያ ጊዜ በመሀከላችን ተገኝተው ቡራኬ መስጠታቸው እንዲሁም የቤዛ ኩሉ የሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶች በብዛት ሆኖ በመሳተፍና ያቀረቧቸው ልዩ ልዩ መዝሙራት እና ሌሎች መንፈሳዊ ዝግጅቶች በልዩ ሁኔታ የሚጠቀሱ ናቸው ::

በተለያዩ ምክንያቶች የበዓሉን አከባበር መርኃግብር በቦታው በመገኘት የበረከቱ ተሳታፊ ለመሆን ላልቻላችሁ ሁሉ ይጠቅማል በማለት የቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶች የሚዲያ ዝግጅት ክፍል ያካፈለንን ፎቶግራፎች ከዚህ በታች አቅርበናል::

የደብራችንን ታላቅነት ባገናዘበ መልኩ የቤዛ ኩሉ የሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶችም ላቀረቧቸው መዝሙራት ፣ ልዩ መንፈሳዊ እና ትምህርታዊ ዝግጅቶች በተጨማሪም ላሳያችሁት መልካም አርአያዊነት ተግባር እያመሰገንን የደከማችሁበት ሁሉ ስለተሳካላችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን:: በዚህ አጋጣሚም  በደብራችን ውስጥ ለሚከናወኑት የሰንበ ት/ቤትና የልጆች ፕሮግራም ተሳታፊዎች: ካህናት: ፕሮግራም መሪዎች: አስተማሪዎች እና ወላጆች ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን። በተጨማሪም የቤዛ ኩሉ የሰንበት ት/ቤት ታዳጊና ወጣቶች የሚዲያ ዝግጅት ክፍልን ለፎቶግራፎቹ እጅግ በጣም እናመሰግናለን::

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
January 24, 2024
Minneapolis, Minnesota, U.S.A.

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

እንኳን ለ2016 ዓ.ም. ከተራ እና ለብርሀነ ጥምቀቱ በስላም አደረሳችሁ!

እንኳን ለ2016 ዓ.ም. ከተራ እና ለብርሀነ ጥምቀቱ በስላም አደረሳችሁ እያለች የፊታችን ቅዳሜ ጥር 11, 2016 (Saturday Jan 20, 2016) ከቀኑ 3 ፒኤም ጀምሮ የከተራ ጉዞ ወደ 6202 Bloomington Road, Fort Snelling, St. Paul, MN 55111 ይደረጋል:: ቀጥሎም እሁድ ጥር 12, 2016 (Sunday Jan 21, 2016) ከቀኑ 1 ኤኤም ጀምሮ በማህሌት: ከቀኑ 5 ኤኤም በቅዳሴ እና ቀጥሎም በታቦት ሽኝት የብርሀነ ጥምቀት በአልን በደመቀ ሁኔታ ቤተክርስቲያናችን ታከብራለች::

በእለቶቹም ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

የጥምቀት በአል የሚከበርበት አድራሻ: 6202 Bloomington Road, Fort Snelling, St. Paul, MN 55111
ስለ ከተራ እና ጥምቀት አከባበር መርኃ ግብር የሚከተለዉን ይመልከቱ!

የጥምቀት ጾም (የጋድ ጾም) :- ጥር 10, 2016 (Friday Jan 19, 2024)
ከተራ :- ጥር 11, 2016 (Saturday Jan 20, 2016)
ጥምቀት :- ጥር 12, 2016 (Sunday Jan 21, 2016) / The Baptism of Christ (Epiphany).

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአስተዳደር ቦርድ
January 14, 2024
Minneapolis, Minnesota, U.S.A.

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በስላም አደረሳችሁ!

በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በስላም አደረሳችሁ እያለች የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 27, 2016 (Saturday January 6, 2024) ከቀኑ 5 ፒኤም ጀምሮ በማህሌት: ቀጥሎም ከምሽቱ 11 ፒኤም ጀምሮ በቅዳሴ የእየሱሰ ክርስቶስን የልደት በአል በደመቀ ሁኔታ ታከብራለች:: በእለቱም ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታቀርባለች::

መቼ: ቅዳሜ ታህሳስ 27, 2016 ከ 5 ፒኤም ጀምሮ
When: Saturday January 6, 2014 from 5pm

ከዚህ በታች ያሉት ፎቶግራፎች የሚያሳዩት የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የ2016 ዓ.ም. የእየሱሰ ክርስቶስ የልደት በአልን በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ሲያከብሩ ነዉ::

የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ውስጥ ከተመሰረተ 27 አመት አስቆጥሯል::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

ጾመ ነቢያት (የገና ጾም): ቅዳሜ ኅዳር 15 ለሚጀመረው እና በረከት ለምናገኝበት ጾመ ነቢያት እንኳን አደረሰን!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤
እንኳን ለጾመ ነቢያት (የገና ጾም) በሠላም አደረሳችሁ።

የኢትዮያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰባት የአዋጅ አጽዋማት ያሏት ሲሆን ከእነዚህ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ የነቢያት ጾም ነው። ጾሙን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከመገለጡና ሰው ከመሆኑ በፊት ነቢያት የጌታን መምጣት በናፍቆት በጾምና በጸሎት ሲጠባበቁ ነበር። ስለዚህ የነቢያትን የጾም ድካም ለማሰብና እንደ ነቢያት መንፈስ ኃይልን ለመልበስ በእምነት ለመጽናት ኃጢአትን ለመዋጋት ሲባል ይህን ጾም እኛ እንጾመዋለን።

ይህንን ጾም በተመለከተ በፍትሐ ነገሥት (ፍትሕ መንፈሳዊ) አንቀጽ ፲፭፥፭፻፷፬ ጀምሮ ተጽፏል። በፍትሕ መንፈሳዊ በአንቀጽ ፲፭፥፭፻፷፰ ላይ እንደተገለጸው ከኅዳር እኩሌታ እስከ ልደት የሚጾመው ጾም ነው።
“መጀመርያው የኅዳር እኩሌታ፡ ፋሲካው፡ የልደት በዓል ነው።” ተብሎ የጾመ ነቢያት መነሻውና መድረሻውን ፍትሐ ነገስት ላይ ተገልጿል። ይህም ማለት በሦስቱ ወንጌላውያን ማለትም በዘመነ ማቴዎስ፣ በዘመነ ማርቆስና በዘመነ ሉቃስ የገና ጾም ከኅዳር ፲፭ ጀምሮ  በኅዳር ፳፱ ይፈሰካል። በዚህ በያዝነዉ በዘመነ ዮሐንስ ደግሞ የገና ጾም ቅዳሜ ኅዳር ፲፭  ተጀምሮ እሁድ ኅዳር ፳፰
ይፈሰካል።

ጾሙን የበረከት ያድርግልን!

ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) :-
ከህዳር 15,2016 አስከ ታህሳስ 28, 2016
(Saturday Nov 25, 2023 – Sunday Jan 7, 2024)

ጽሁፉን ያዘጋጀችው ወይዘሮ ሐና ስዩም ነች::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

የኅዳር ሚካኤልን በዓለ ንግስ በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያክብሩ!

የኅዳር ሚካኤል በዓለ ንግስ እሁድ ህዳር 9, 2016 በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በደመቀ ሁኔታ ይከበራል:: መጥተው የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች::

መቼ? / When?
እሁድ ህዳር 9, 2016 ከ2:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ
Sunday Nov. 19, 2023 from 2:00 am

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአስተዳደር ቦርድ

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406 ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
Website: https://www.debreselam.net

በፌስቡክ እንዲከተሉን ይህን ይጫኑ / Click Here to Follow Us On Facebook

የ2016 የአመታዊ፣ የንግሥ በዓላት እና የአጿማት ቀን መቁጠሪያ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤
የ2016 አ.ም. ከገባ የመጀመሪያውን ወር አገባድደናል:: አዲስ አመት እንደመሆኑም የአመታዊ፣ የንግሥ በዓላት እና የአጿማት ቀን አቆጣጠሩ ላይ ብዙ ማወቅ የምትፈልጉት እንዳሉ እንገነዘባለን:: ለምሳሌም ያህል የጾም ቀኖች እና ወራቶች የትኞቹ ናቸዉ? የአመታዊ እና የንግሥ በዓላት የሚዉሉባቸዉ ቀኖችስ የትኞቹ ናቸዉ? በዩኤስ ባንክ ስታዲየም ለአዲስ ቤተክርስቲያን ማሰሪያ የሚውል የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ቀኖች እና ወራቶችስ የትኞቹ ናቸዉ? የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የህጻናት ታዳጊዎችና ወጣቶች አገልግሎት መርኃ ግብሮች መቼ መቼ ሊውሉ እንደሚችሉ እቅድ እና ፕሮግራም ወጥቶላቸዋል? ይህ
የቀን መቁጠሪያ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልሰ ይሰጣል:: ስለሆነም ከወዲሁ በመዘጋጀት ከመላዉ ቤተሰብ፣ ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተካፊይ እንዲሆኑ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

  • ማሕሌተ ጽጌ / ወርሃ ጽጌ (የፍቃድ ጾም ነው) : ከመስከረም 26, 2016 እሰከ ህዳር 6, 2016 (Sat Oct 7, 2023 – Thurs Nov 16, 2023)
  • የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- ጥቅምት 12, 2016 (Mon Oct 23, 2023) / U.S. Bank Stadium volunteer work
  • መንፈሳዊ ጉባኤ :- ጥቅምት 17, 2016 (Saturday Oct 28, 2023) ከ3:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ. በጉባኤ አዳራሽ 1040 Osborne Road NE, Fridley MN 55432)
  • መንፈሳዊ ጉባኤ :- ጥቅምት 18, 2016 (Sunday Oct 29, 2023) ከ4:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
  • መንፈሳዊ ጉባኤ :-ጥቅምት 22, 2016 (Thursday Nov 2, 2023) ከ5:00 ፒ.ኤም.. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
  • መንፈሳዊ ጉባኤ ;_ ጥቅምት 24, 2016 (Saturday Nov 4, 2023) ከ4:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
  • ጥቅምት መድሐኔዓለም :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : ጥቅምት 25, 2016 (Sunday Nov 5, 2023)
  • የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- ኅዳር 2, 2016 (Sunday Nov 12, 2023) / U.S. Bank Stadium volunteer work 
  • ኅዳር ሚካኤል :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : ህዳር 9, 2016 (Sunday Nov. 19, 2023) / Hidar St. Michael
  • ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) :- ከህዳር 15,2016 አስከ ታህሳስ 28, 2016 (Saturday Nov 25, 2023 – Sunday Jan 7, 2024)
  • የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- ኅዳር 17, 2016 (Monday Nov 27, 2023) / U.S. Bank Stadium volunteer work
  • የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- ታኅሳስ 14, 2016 (Sunday Dec 24, 2023) / U.S. Bank Stadium volunteer work
  • ታኅሳስ ገብርኤል :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : ታኅሳስ 21, 2016 (Sunday Dec. 31, 2023) / Tahisas St. Gabriel
  • የበጎፈቃደኝነት አገልግሎት በዩኤስ ባንክ ስታዲየም :- ታኅሳስ 21, 2016 (Sunday Dec 31, 2023) / U.S. Bank Stadium volunteer work
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የልጆች የገና በዓል ዝግጅት :- ታኅሳስ 26, 2016 (Friday Jan 5, 2024)
  • ልደት (ገና) :- ታኅሳስ 28, 2016 (Monday Jan 7, 2024) / The Birth of Christ
  • የጥምቀት ጾም (የጋድ ጾም) :- ጥር 10, 2016 (Friday Jan 19, 2024)
  • ከተራ :- ጥር 11, 2016 (Saturday Jan 20, 2016)
  • ጥምቀት :- ጥር 12, 2016 (Sunday Jan 21, 2016) / The Baptism of Christ (Epiphany).
  • የካቲት ኪዳነምሕረት :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : የካቲት 17, 2016 (Sunday Feb. 25, 2024) / The Covenant of Virgin Mary.
  • ጾመ ነነዌ :- የካቲት 18, 2016 (Monday Feb 26, 2024)
  • የዓብይ ጾም (የሁዳዴ ጾም) :- ከመጋቢት 2 አስከ ሚያዝያ 27 (Monday March 11, 2024 – Sunday May 5, 2024)
  • መጋቢት መድሐኔዓለም :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : መጋቢት 29, 2016 (Sunday Apr. 7, 2024) / Megabit Medhanealem / The original Crucifixion.
  • ደብረ ዘይት :- መጋቢት 29, 2016 (Sunday April 7, 2024) / Debrezeit
  • ሀሳዕና :- ሚያዝያ 20, 2016 (Sunday April 28, 2024) / Hosanna
  • ሰሙነ ሕማማት :- ሚያዝያ 21, 2016 እስከ ሚያዝያ 26, 2016 (Monday April 29, 2024 to Friday May 3, 2024) / Holy/Passion week.
  • ጸሎተ ሐሙስ :- ሚያዝያ 25, 2016 (Thursday May 2, 2024) / Maundy Thursday
  • ስቅለት :- ሚያዝያ 26, 2016 (Friday May 3, 2024) / Good Friday (Crucifixion)
  • ትንሣኤ :- ሚያዝያ 27, 2016 (Sunday May 5, 2024) / Easter
  • የእመቤታችን ልደት በአል :- ግንቦትt 1, 2016 (Thursday May 9, 2024) / The Birthday of Virgin Mary
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት ለህጻናት ታዳጊዎችና ወጣቶች የሰመር ኮርስ :- ሰኔ 10,-ሰኔ 21 2016 (June 17, 2024 – June 28,2024) / Kids summer course
  • እርገት :- ሰኔ 6, 2016 (Thursday June 13, 2024) / Ascension. The day of Holy Spirit (Pentecost)
  • ሰኔ ሚካኤል :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : ሰኔ 9, 2016 (Sunday June 16)/ Sene St. Michael.
  • ጴራቅሊጦስ :- ሰኔ 16, 2016 (Sunday June 23, 2024) / Peraklitos
  • ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) :- ከሰኔ 17, 2016 እሰከ ሀምሌ 5, 2016 (Monday June 24, 2024 – Friday July 12, 2024)
  • ጾመ ድህነት :- ሰኔ 19, 2016 (Wednesday June 26, 2024)
  • በአለ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ወገብረመንፈስ ቅዱስ (አቦ በአል) :- ሐምሌ 5, 2016 (Friday July 12, 2024) / The Martyrdom of Peter and Pau
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የልጆች ሰመር ካምፕ :- ከሀምሌ 8, 2016 እስከ ሀምሌ 12, 2016 (Monday July 15, 2024 – July 19, 2024) / kids summer camp
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የህፃናት ከ12 አመት በታች የመዝናኛ እና የሽርሽር ጉዞ :- ሐምሌ 18, 2016 (Thursday July 25,2024) / Field Trip for children under 12 years old
  • ሐምሌ ገብርኤል :- በዓለ ንግሱ መርኃ ግብር የሚከናወንበት ትክክለኛ ቀን : ሐምሌ 21, 2016 (Sunday July 28, 2024) /  Hamle St. Gabriel.
  • የቤዛ ኩሉ ስንበት ት/ቤት የታዳጊና የወጣቶች (teenagers ) ከ13 አመት በላይ የመዝናኛ እና የሽርሽር ጉዞ :- ሐምሌ 20, 2016 (Saturday July 27, 2024) / Field Trip for youth over 13 years old
  • ጾመ ፍልሰታ :- ከነሀሴ 1, 2016 እስከ ነሀሴ 16, 2016 (Wed August 7, 2024 – Thursday Aug 22, 2024)
  • ደብረ ታቦር :- ነሐሴ 13, 2016 (Monday August 19, 2024) / Transfiguration (Debre Tabor)
  • ነሐሴ ኪዳነምሕረት :- ነሐሴ 16, 2023 (Thursday August 22, 2024) / The assumption of Virgin Mary.

ለዚህ የቀን መቁጠሪያ ዝግጅት መሳካት የተባበሩኝን ወይዘሮ ሀና ስዩምን: አቶ ደረሰ ለማን እና አቶ ጌታቸው ደበበን አመስግኑልን:: እኛም እጅግ በጣም እናመሰግናለን::

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአስተዳደር ቦርድ
October 15, 2023
Minneapolis, Minnesota, U.S.A.

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ኢሜይል: membersservice@dsmachurch.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ይደረጋል!

  • መንፈሳዊ ጉባኤ :- ጥቅምት 17, 2016 (Saturday Oct 28, 2023) ከ3:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ. በጉባኤ አዳራሽ 1040 Osborne Road NE, Fridley MN 55432
  • መንፈሳዊ ጉባኤ :- ጥቅምት 18, 2016 (Sunday Oct 29, 2023) ከ4:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
  • መንፈሳዊ ጉባኤ :-ጥቅምት 22, 2016 (Thursday Nov 2, 2023) ከ5:00 ፒ.ኤም.. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
  • መንፈሳዊ ጉባኤ ;_ ጥቅምት 24, 2016 (Saturday Nov 4, 2023) ከ4:00 ፒ.ኤም. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
  • ጥቅምት መድሐኔዓለም :- ጥቅምት 25, 2016 (Sunday Nov 5, 2023) ከ2:00 ኤ.ኤም. ጀምሮ በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን

ከዘመድ እና ከወዳጅ ጋር በመምጣት የበረከቱ ተካፊይ እንዲሆኑ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአስተዳደር ቦርድ
October 15, 2023
Minneapolis, Minnesota, U.S.A.

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ኢሜይል: membersservice@dsmachurch.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/

እንኳን ለ፳፻፲፮ ጽጌ ማሕሌት በሠላም አደረሳችሁ። /October 7, 2023 – November 16, 2023/

የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤
እንኳን ለማሕሌተ ጽጌ በሠላም አደረሳችሁ።
ፅጌ ማለት አበባ ማለት ሲሆን ፀገየ ከሚለው የግዕዝ ቃል የመጣ ነው። ጽጌ ማሕሌት በየአመቱ ከመስከረም ፳፮ እስከ ህዳር ፮ (Oct 7, 2023 – Nov 16, 2023)
፵ ቀናት ወይም ፩ ወር ከ ፲ ቀን የሚቆይ ነው። ጽጌ ማሕሌት እመቤታችን ጌታችንን ይዛ መሰደዷን መራቧን መጠማቷን በማሰብ ነው

በማሕሌተ ጽጌ ወቅት ያሉት ሳምንታት ውብ ናቸው ምክንያቱም :-
☞እማምላክን ከነልጇ እንለምንበታለን ስደቷን እናስብበታለን፣
☞ የእመቤታችንን ፍቅሯን እናትነቷን አማላጅነቷን ከሊቃውንቱ ጋር ሆነን በዝማሬ እናወድስበታለን ፣

ጽጌ ማሕሌት የፈቃድ ፆም ስትሆን ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ብቻ ይፆሟታል። ምንም እንኳን ፆመ ፅጌ ከ ፯ ቱ የአዋጅ አፅዋማት መካከል ባትሆንም እና እንድንፆማት በአዋጅ ባንታዘዝም በፈቃዳችን በመፆማችን ከፆሟ ረድኤት በረከት የምናገኝባት ነች።

ሰንበትን ከጌታ ከኢየሱስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ሌሊቱን በምስጋና በያሬዳዊ ዜማ ሳምንቱን ደግሞ በፈቃዳችን ማንም ሳያዘን የድንግል ማርያም ፍቅሯ አክብረን እንጾማለን።

እንኳን ለዚህ ጊዜ አደረሰን አደረሳችሁ !!!
የእመቤታችን ፍቅሯ ይብዛልን::

ጽሁፉን ያጠናቀረዉ አቶ ኤልያስ ወርቅህ ነዉ::

አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ኢሜይል: membersservice@dsmachurch.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/