የሚኒያፖሊስ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የትንሳኤ አገልግሎት ቀጥታ ስርጭት – ስርጭቱን ለመከታተል ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
Easter Live Broadcasting
የሚኒያፖሊስ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የትንሳኤ አገልግሎት ቀጥታ ስርጭት – ስርጭቱን ለመከታተል ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
Easter Live Broadcasting
የሚኒያፖሊስ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የስቅለት አገልግሎት ቀጥታ ስርጭት – ስርጭቱን ለመከታተል ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
Good Friday Live Broadcasting
ምንም እንኳ ይህ ጥያቄ በብዙ ሰዎች ዘንድ የተመለሰ ቢሆንም ተደጋጋሚ ጥያቄዎች መምጣታቸው ሁለት ነገሮችን ስላመለከተኝ እኔም እንደገና በአጭሩ ለመመለስ ጥረት አደርጋለሁ፡፡ የመጀመሪያው የተሰጠው መልስ ለሁሉም እኩል አለመድረሱ ሲሆን በሁለተኛነት ደግሞ አንዳንዶቻችንም ተደጋሞ አንድ ዓይነት መልስ በማየት የማረጋገጥ ፍላጎት ያለን ይመስላል፡፡
ይህን የመሰሉ ተደጋጋሚ ጥቄዎች ሲገጥሙን ነገሩን ማየት ያለብን ከመሠረታዊው የቤተ ክርስቲያን ትውፊትና አስተምህሮ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ ይህ ጥያቄ የበዓሉን አከባበር የሚመለከት ስለሆነ በቤተ ክርስቲያናችን የበዓላት ቀኖናም ሆነ ትውፊት መሠረት በዓላት የሚበላለጡ ከሆነ የሚበልጠው የትኛው ነው ከሚለው ቀላል ጥያቄ ልንነሣ እንችላለን፡፡ በዚሁ መሠረት የመጀመሪያውን ደረጃ የሚይዙት የጌታችን ዐበይት በዓላት ቀጥሎም የጌታችን ንዑሳት በዓላት መሆናቸውን ለመረዳት አያስቸግርም፡፡ Continue reading በዓለ ስቅለት እና በዓለ እግዝእትነ ሲገጣጠሙ ይሰገዳል ወይስ አይሰገድም?
Learn to Prepare Taxes and Make a Difference at the same time. How can you make a difference? Simple. Help your community in preparing taxes free of charge or for a voluntary contribution to building funds by becoming a volunteer with the Free Income Tax Preparation Service Initiative.
Be a Volunteer. This Free Income Tax Preparation Initiative is a partnership between Amare Berhie and your church, Debreselam Medhanealem Church.
Volunteers typically start training in January. They are expected to provide two to three hours (Sunday) of service per week between the beginning of February to the middle of April. The time commitment will vary depending on individual responsibilities as well as the number of volunteers working at a site and the number of people being served by the site.
Volunteer Requirements:
Why Volunteer?
Great volunteers are the key to our success. Join this year’s effort and help make a difference in our community.
Want More Information?
Call 651-235-5341
Get Your Tax Refund Fast!!!
Combining e-file with direct deposit is the fastest and safest way to get your refund. Amare Berhie, an IRS licensed Enrolled Agent and an Authorized e-file Provider, is providing free tax preparation services in hopes of raising funds for Debreselam Medhanealem EOTC building. You are welcome to make donations of any amount. Please come and take advantage of this offer to have your taxes completed by an experienced professional and your voluntary contribution will go to a good cause.
ነጻ የገቢ ታክስ ዝግጅት አገልግሎት
ከገቢ ታክስ ተመላሽ ክፍያ በተፋጠነ መንገድ ለማግኘት ሰነዱን በአሌክትሮኒክስ ገቢ በማድረግና ተመላሹ ገንዘብ ለባንክ በቀጥታ ገቢ እንዲሆን የሚያስችል የታክስ ዝግጅት አገልግሎት ባሁኑ ወቅት በቤተክርስትያናችን ይሰጣል።
ለቤተክርስትያን ህንጻ ግንባታ ገንዘብ ለማሰባሰብ እንዲረዳ በማቀድ ለዚሁ ሙያ ህጋዊ ፈቃድና የምስክር ወረቀት ያላቸው ባለሙያ አቶ አማረ በርሄ ለግል ድካማቸው ክፍያ ሳይጠይቁ አገልግሎቱን ለመስጠት ተዘጋጅተዋል። ለዚህም በጎ ተግባር አቅማችሁ የቻለውን ያህል በመለገስ ሰፊ የሥራ ልምድ ባለው ባለሙያ በአገልግሎቱ እንድትጠቀሙ ቤተክርስትያናችን ትጋብዛለች።
Get Your Federal, State & Property Tax Refund Fast!!!
Free Income Tax Preparation Service Initiative – we offer Federal and State tax preparation with secure electronic filing and direct deposit.
Get Your Taxes Done For Free Or Voluntary Contribution To The DSMA EOTC Building Fund.
Get your refund the fastest way possible using e-file and direct deposit. We’ll help you get all the credits you qualify for and file your return electronically, so you’ll get your refund fast.
What Should I Bring?
Additional Tax Information/Forms
Do I Need To Make An Appointment?
Appointments are appreciated but walk-ins are welcome! Our Program runs from January to April 15, 2016, Sunday 9:00 to 11:30pm.
About Our Program:
This Tax Preparation Volunteers program is a partnership between Amare Berhie & Debreselam Medhaniealem EOT Church and is operated by volunteers.
About Amare Berhie:
Amare Berhie, Enrolled Agent, founder & CEO of ABA Tax Accounting, a public accounting firm and AB Tax Online, FREE e-Filing Tax Service is a Tax & Accounting professional and real estate investment consultant. IRS licensed and authorized by the United States Department of Treasury to appear on taxpayers behalf at all levels of the IRS, in ALL States and an Authorized IRS e-file Service Provider.
What are the limitations to services?
We can help most people with their tax returns, but some returns are too complex for this engagement. Here are services we do NOT provide:
Note: For complex or out of scope returns, you may contact Amare Berhie at ABA Tax Accounting or other professional preparers for assistance.
What If I want To File For Free On My Own?
If you’d prefer to file online on your own, you may visit AB Tax Online. Federal tax is free for those who made less than $100,000 in 2015, single or married filing joint.
የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመስራቾቹ አንዱ እና ታላቅ አባት የነበሩት አቶ ታዬ ረታ ባደረባቸው ህመም ሲረዱ ቆይተው በትላንትናው እለት በፌርቪው ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል አርፈዋል።
ቤተ ክርስቲያናችን የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸች ለልጆቻቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው ሁሉ መጽናናት ትመኛለች። እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ከደጋጎቹ አባቶች ጎን ያሳርፍልን።
የእዝኑ ቦታ: Lao Community Center 320 University Ave W Saint Paul MN, Thursday and Friday from 2 PM
ሥርዓተ ፍትሃት: ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም 4401 Minnehaha Ave S MPLS MN 55406 -Saturday @10AM
ስርዓተ ቀብሩ: Sunset Funeral Chapel – 2250 St Anthony Blvd, Minneapolis, MN 55418
በታላቁና በአንጋፋው በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያ 3ኛው ዙር የመጀመሪያው ቀን መንፈሳዊ ጉባዔ ልዩ መንፈሳዊነት በያዘ መልኩ ትላንት በደብሩ ካህናቶች በጸሎት ተከፍቷል። ይህ ለ3 ተከታታይ ቀን የሚቆየው ጉባዔ ላይ ቤተክርስቲያን ካፈራቻቸው የወንጌል ሰባክያን መሀከል ለመናፍቃን በቂ መልስ በመስጠት የሚታወቀው መምህር ምሕረተአብ አሰፋ የወንጌል አገልግሎት ሰጥተዋል። መምህር ምሕረተአብ መቀመጫቸውን በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም በማድረግ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች በሲያትል፣ በዳላስ ፣ በአትላንታ፣ በዴንቨር ያደረጉት አገልግሎት በእግዚአብሔር ፈቃድ የተሳካ ሆኗል። በትላንትናው እለት በደብራችን የተጀመረው የሶስተኛውን ዙር ጉባዔ በመምህር ምሕረተአብ የስብከተ ወንጌል እና የዝማሬ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን በዚህ ጉባዔ ላይ ተጋባዥ እንግዳ የሆኑት ወንድማችን ጥላሁን (ከዲሲ) ዝማሬውን በክራር በማጀብ ጉባዔውን ልዩ እንዲሆን አድርገውታል። በመጨረሻም ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ጸሎተ ምህላ ተደርጎ የትላንትናው መርሃ ግብር በጸሎት ተዘግቷል። ይህ ጉባዔ ቅዳሜና እሁድ የሚቀጥል ሲሆን በዚህ አጋጣሚ አገልግሎቱ ላይ ተገኝተሁ የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች።
ክብር እና ምስጋና ለድንግል ማርያም ልጅ ለእርሱ ለሀያሉ አምላካችን ይሁን።
የማይቀርበት ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በአናጋፋውና በታላቁ ደብር በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መቀመጫውን ሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አድርጎ የሥብከተ ወንጌልን እሳት በዚህ ታላቅ ደብር ለኩሶ በምድረ አሜሪካ እያቀጣጠለ ያለው ታላቁ የተዋህዶ የወንጌል ገበሬ በመምህር ምህረተዓብ አሰፋ December 18, 19 and 20 ከ5 pm እስከ 8pm።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር !
ዜና ደብረሰላም መድኃኔዓለም ዘሚኒሶታ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
የሜኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ቤተክርቲያን ዓመታዊውን የጥቅምት መድኃኔዓለም ክብረ በአል ብጹእ አቡነ አትናቴዎስ የደቡብ ወሎና በአማራ ክልል የኦሮሞ ሕብረተሰብ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብጹእ አቡነ ዳንኤል የድሬዳዋና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ታዋቂው ሰባኪ ወንጌል መምህር ምሕረተአብ አሰፋ በተገኙበት በትላንትናው እለት እጅግ በደመቀና ባመረ ሥነ ስርዓት ተከብሮ ውሏል።
በዚህ ቁጥሩ ከምንግዜውም በላይ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ በተገኘበት በአለ ንግሥ ላይ ከዋዜማው ጀምሮ ሰፊ መንፈሳዊ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን ብጹአን አባቶችም ለታዳሚው ሕዝብ ትምህርት፣ ቡራኬና ቃለ ምእዳን ሰጥተዋል።
ብጹእ አቡነ አትናቴዎስ የደቡብ ወሎና በአማራ ክልል የኦሮሞ ሕብረተሰብ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት አባታዊ ቃለ ምእዳን እና ቡራኬ የሜኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አንዳንዶች እንደሚናገሩት ከእናት ቤተክርስቲያን የተለ ሳይሆን ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ ነው። አንዳንዶች እንደሚሉት ይህ ባይሆን ኖሮ እኛም የምንወዳቸውን እና የምናከብራቸውን ምእመናን መጥተን ባልባረክናችሁ ነበር ብለዋል። ብጹእነታቸው እንዳሉት እንደ አባቶቻችን ሕግና ሥርአት እምነት አንድ ነው ጥምቀትም አንድ ነው ምናልባት በእምነት የመሰነካከል ነገር እንኳን ቢኖር ለዚያም የተሰራ ሥርዐት አለ ከዛ ውጪ ግን አንድ ግዜ የተሰጠን ጥምቀት መከለስ አይቻልም፤ በጥምቀት ላይ ጥምቀት ቢፈጸም ግን እንደሻወር ነው የሚቆጠረው በማለት በብጹእ አቡነ ዘካርያስ እየተፈጸመ ያለውን ከሕገ ቤተክርስቲያን የወጣ ድርጊት የተሳሳተ መሆኑን አመልክተዋል።
ብጹእ አቡነ ዳንኤል የድሬዳዋና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ በበኩላቸው የእለቱን በአል የተመለከተ ትምህርት ከሰጡ በኃላ በተለይም ጥምቀትን አስመልክቶ በሰጡት ትምህርት ይልቁንም ሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያናት በጥንቃቄ የሚፈጸሙ እንደሆኑ አስረድተው ሚስጢረ ጥምቀትና ምስጢረ ክህነት ፈጽሞ የማይደገሙ መሆናቸውን ተናግረዋል። ብጹእነታቸው እንዳሉት ጥምቀትን የሚደግም ማንም ቢኖር የቤተክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ እና አባቶች ፍጹም ርምጃ ይወስዳሉ ሲሉ አስገንዝበዋል። ይህ ክርስትና እንደገና የማንሳትን ተግባር እውነተኛ ኦርቶዶክስ የሆነና ህሊና ያለው ሰው በፍጹም የሚያደርገው ነገር አይደለም ካሉ በኋላ በሌላ ነገር መቀየም ይቻል ይሆናል ይህን ማድረግ ግን ከባድ ቅጣት የሥልጣነ ክህነት መያዝና ውግዘት እንደሚያስከትል አብራርተዋል።
ስለ ሜኒሶታ ደብረሰላም ቤተክርስቲያንም ሲመሰክሩ ይህች ቤተክርስቲያን በብዙ አንጋፋ ብጹአን አባቶች የተባረከች ስለሆነች ምንም አይነት ቅሬታ እና መጠራጠር እንዳይሰማችሁ እናረጋግጥላችኋለን ከዚህች ቤተክርስትያን ወዴትም እንዳትሔዱ እናሳስባችኋለን በማለት ምእመናንን የሚያጽናና እና የሚያንጽ ቃለ ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡ ወደዚህ ስንመጣ ምንም አይመስለንም ደስ እያለን ነው የምንመጣው፤ ከዚህ ከወጡት ልጆቻችን ጋርም ሰላምንም ለማምጣት ብዙ ጥረናል አሁንም እየጣርን ነው ብለዋል። ብጹእ አባታችንም /ብጹእ አቡነ አትናቴዎስ/ ብዙ ጥረዋል፤ ሰላም ለማምጣት ስልክ ደውለው ጆሯቸው ላይ ነው የዘጉባቸው ይህን ግፍ እግዚአብሔር እንዳይቆጥርባቸው እንጸልይላቸዋለን ብለዋል።
ቀደም ሲልም መምህር ምሕረታብ አሰፋ ሰፊ የሆነ የወንጌል ትምህርት የሰጡ ሲሆን በማስከተልም ቤተክርስቲያኑ ላለበት የተለያዩ ወጪዎች እና ወደፊት ለመስራት ላቀደው አዲስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ በእለቱ በተደረገ የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጅት 90ሺህ /ዘጠና ሺህ/ ዶላር ያህል ከምእመናን በጥሬ ገንዘብ በቼክና በቃል መግቢያ ቅጽ ተሰብስቧል።
ስላደረገልን ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን።
በጉባኤው ላይ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የድሬደዋና የአካበቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተገኝተው ቡራኬያቸውን ይሰጡናል ።
በኢትዮጵያ እና በመላው አለም በስባኪ ወንጌልነቱ ታላቅ ዝናና ያተረፈው ወንድማችን መምህር ምሕረተአብ አሰፋ ከፊታችን ኃሙስ ጀምሮ ታላቅ የወንጌል ዘር ሊዘራ ተዘጋጅቷል። ዕለቱም ጥቅምት 26 እና 27, 2008 ሐሙስ እና አርብ ከ400PM ጀምሮ (Nov 5 & 6) ሲሆን ቦታውም በMinnehaha Academy “3100 West River PKWY Minneapolis MN 55406″ ሚኒሶታም በወንጌል ስትናወጽ ታመሻለች – ወንጌል እንዳይሰበክ የሚቅበዘበዘው ዲያቢሎስም ድል ይመታል። ቅድስት እናታችን እመብርሃንም ከፈ ከፍ ትላለች። ታዲያ በዚህን ዕለት እንኳን መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል።
ቦታ
Minnehaha Academy
3100 West River PKWY
Minneapolis MN 55406
ከሚኒያፖሊስ
Lake Streetን ይዘው ወደ ሴይንት ፖል ሲጓዙ 46ኛው ጐዳና ላይ ወደ ቀኝ ታጥፈሁ አስከ 32ኛው መንገድ ይሁዱ፤ Minnehaha Academyን 46 እና 32 ላይ ያገኙታል
ከሴይንት ፖል
Lake Streetን ይዘው ወደ ሚኒያፖሊስ ሲጓዙ 46ኛው ጐዳና ላይ ወደ ግራ ታጥፈሁ አስከ 32ኛው መንገድ ይሁዱ፤ Minnehaha Academyን 46 እና 32 ላይ ያገኙታል
ብፅዕ አቡነ አትናቴዎስ እና መምህር ምሕረተአብ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሽኝት ሲደረግላቸው የሚያሳይ ፎቶ ግራፍ
ታላቅ የምስራች“እግዚአብሔር ስለእናንተ ይዋጋል እናንተም ዝም ትላላችሁ።” ዘጸ.14፥14
ሁሉንም ነገር በጊዜው የሚያከናውን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ሆኖ አባታችን ብጹእ አቡነ አትናቴዎስ የደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሊባርኩንና ቃለ ምእዳን ሊሰጡን ለሁለተኛ ጊዜ በደብራችን ይገኛሉ። እንዲሁም መምህር ምሕረተአብ አሰፋ በቤተክርስቲያናችን ለመጀመርያ ጊዜ ተገኝተው ሰፊ የወንጌል አገልግሎት ሊሰጡን ከብጹእ አባታችን ጋር ከቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ ጉዟቸውን ጀምረዋል።እንደ እግዚአብሔር ፈቃድም ብጹእ አባታችን እና መምህር ምሕረተአብ ማክሰኞ ኦክቶበር 27/2015 ዓ.ም ከምሽቱ 6፡30PM ላይ በቤተክርስቲያናችን ደማቅ አቀባበል የሚደረግላቸው ስለሆነ ይህን መልእክት ያነበባችሁ የሚኒያፖሊስና አካባቢዋ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ሁላችሁም በደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በመገኘት ከብጹእ አባታችን በረከትን እንድታገኙ ስንል ይህን አስደሳች ዜና በደስታ እናስተላልፋለን።የመጀመርያ ቀን የወንጌል ትምሕርት መርሐግብርም የፊታችን ሐሙስ ኦክቶበር 29/2015 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30PM ጀምሮ በደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ ክርስቲያን በመምህር ምሕረተአብ አሰፋ የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ እናስውቃለን።“እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።” ዘጸ 15፥ 3