የተከበራችሁ የቤተክርስትያናችን አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ፤
እንደወትሮው ሁሉ የሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባላት እና ቤተሰቦቻቸው አዲስ የቤተክርስቲያን ሕንፃ ለመገንባት የሚያስፈልገውን የገንዘብ ወጪ በከፊል ለመሸፈን ያስችል ዘንድ ከኪሳችን ከምናዋጣው በተጨማሪ በ2023 ዓ.ም. የበጎፈቃደኝነት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ በዩኤስ ባንክ ስታዲየም እና በሚኔሶታ ስቴት ፌር ተስማርተን ነበር :: እንደምታስታውሱት ሁሉ የመጨረሻው የበጎአድራጎት የስራ ቀን የተጠናቀቀው ያለፈዉ ወር እሁድ December 31, 2023 በዩኤስ ባንክ ስታዲየም ውስጥ በተደረገው የቫይኪንግ እና የግሪን ቤይ ፓከርስ ቡድኖች ጨዋታ ቀን ነበር:: ይህን የስራ ዘርፍ ከጀመርን እነሆ ሰባት አመታትን አአስቆጥረናል! ስለሆነም ባለፈው አመት ውስጥ ስለተከናወኑት የበጎአአድራጎት ስራዎች እና ስለተስበስበው የገንዘብ መጠን ለግንዛቤ ይረዳል ተብሎ በበጎአድራጎት ስራ አስተባባሪዎቹ በኩል የተዘጋጀ አጭር ሪፖርት ከዚህ በታች ባለው መልኩ ቀርቧል::
በ2023 ዓ.ም. ስንት የበጎፈቃድ አገልግሎት ሰራ ቀኖች ነበሩ?
በአመቱ በጠቅላላው 27 የበጎፈቃድ አገልግሎት ሰራ ቀኖች ነበሩ:: እነሱም 11 የቫይኪንግ ጨዋታዎች ፣ 10 በሚኒሶታ ስቴት ፌር የመክና ማቆሚያ ማስተናገድ ስራ እና 6 በዩእስ ባንክ ስታዲየም በተደረጉ የሙዚቃ ኮንስርቶች እና ሞንስተር ጃም ትእይንቶች ነበሩ:: በ2023 በተደረጉት ስራዎች አንድ የበጎአድራጎት የስራ ቀን በአማካይ ከ 7 እስክ 9 ሰአቶች ይፈጅ ነበር::
በ2023 ዓ.ም. የበጎፈቃድ አገልግሎት ሰራ ላይ ስንት አባላት ፣ ቤተስቦችና ወዳጆች ነበሩ?
በዚህ አመት በጠቅላላው 111 የደብራችን አባላት ቤተስቦችና ወዳጆች በበጎአድራጎት ሰራ ላይ ተስማርተው ነበር:: ከ 7-14 ቀኖች የስሩ 10 እባላት ፣ ከ4-5 ቀኖች የሰሩ ሌሎች 10 እባላት ፣ ከ 2-3 ቀኖች የስሩ 36 አ ባላት ፣ እንዲሁም አንድ ቀን ብቻ የስሩ 55 አባላት ነበሩ::
የስሩበት ቀኖች ብዛት | የስሩ አባላት ብዛት | % |
7 – 14 | 10 | 9% |
4 – 5 | 10 | 9% |
2 – 3 | 36 | 32% |
1 | 55 | 50% |
ጠቅላላ | 111 | 100% |
በ2023 ዓ.ም. የበጎፈቃድ አገልግሎት ሰራ ላይ እነማን ነበሩ?
በ2023ዓ.ም በተደረገው የበጎአድራጎት ስራ ወቅት ከ4 እስከ 14 ቀኖች ያገለገሉ 20 አባላት ስም ዝርዝር እና የስሩባቸው ቀኖች ብዛት በሚከተለው ሰንጠረዥ ላይ ተቀምጧል:: በዚህ አመት ብቻ 14 የበጎአድራጎት የስራ ቀኖችን በመስራት ከፍተኛውን ደረጃ የወሰደው የፕሮግራሙ አስተባባሪ ዶ/ር አሻርግሬ አትሬ ነው::
የ አባል ስም | የስሩበት ቀኖች ብዛት |
ዶ/ር አሻግሬ አትሬ | 14 |
ወ/ሮ በስልፍዋ መንገሻ | 11 |
ወ/ሮ አባይነሽ ደበላ | 10 |
ዶ/ር ብርሀኑ በለጠ | 10 |
አቶ ዳንኤል ከህሉ | 9 |
ዶ/ር መስፍን ተስፋዬ ገባያው | 9 |
አቶ አለምሰገድ ተስፋዬ | 8 |
አቶ እሸቱ ባዱንጋ | 8 |
አቶ ኤልያስ ጥላሁን | 7 |
አቶ ግርማ መኮንን | 7 |
አቶ አማረ በርሄ | 5 |
አቶ አሸናፊ ቡልቶ | 5 |
አቶ ፀጋ በዛብህ | 5 |
አቶ አበራ በርጃ | 4 |
አቶ ደረጀ አለሙ | 4 |
አቶ ደረስ ገ /ጊዬርጊስ | 4 |
ወ/ሮ እጅጋየሁ ይርጉ | 4 |
አቶ ገዛኸኝ ዳምጤ | 4 |
ወ/ሮ ራሄል ባልቻ | 4 |
ወ/ሮ ትእግስት መለሴ | 4 |
በ2021ዓ.ም. ፣ በ2022 ዓ.ም. እንዲሁም በ2023 ዓ.ም. የበጎአድራጎት ስራ የስሩትን አባላት ስም ዝርዝር እና የስሩባቸውን ቀኖች ብዛት ለማየት የሚከተለዉን ሊንክ ይጫኑ! https://mesfinbcc.pythonanywhere.com/
በ2023 ዓ.ም. የበጎአድራጎት ስራ ምን ያህል ገንዘብ ተስበስበ?
በዚህ 2023 ዓ.ም. በበጎአድራጎት ስራ ለቤተክርስቲያን ማስሪያ የተስበስበው $56,166 ነበር :: በዚህ አመት በበጎአድራጎት ስራ ያስገባነው የገንዘብ መጠን ካለፉት ሁለት አመታት ስርተን ካገኘነው ጋር ሲነጻጸር እጅግ ያንሳል:: ክዚህ በታች ያለው ግራፍ እንደሚያሳየው በ2022 ዓ.ም. $199,950 እና በ2021 ዓ.ም. $223,558 አስባስበን ነበር::
በሰባት አመታት የበጎአድራጎት ስራ ለቤተክርስቲያን ማስሪያ የተስበስበው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን ስንት ደረስ?
እስከአሁን ድረስ ለቤተክርስቲያን ማስሪያ በበጎአድራጎት ስራ የተስበስበው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን $811,312 ነው:: ዝርዝሩ ከዚህ በታች ተቀምጧል::
እንደምታዉቁት ሁሉ ትልቁ ጉልበታችንና እቅማችን በሁሉም መስክ የተጠናከረ እና የተሳተፈ የአባላት ጥንካሬ ሲኖረን ነው:: ስለዚህም በ2024ዓ.ም. ሁላችንም በምንችለው እውቀት ፣ ጊዜ ፣ ጉልበት እና ገንዘብ በመረባረብና በመደጋገፍ አዲሱን ቤተክርስትያን አስርተን ለመገኘት ያበቃን ዘንድ እንትጋ: : በዚህ አጋጣሚ ሁላችሁም እከአሁን እና ወደፊትም ለምታደርጉት ትብብርና እርዳታ ሁሉ በረከቱ ይብዛላችሁ::
በሚኒሶታ የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
January 30, 2024
Minneapolis, Minnesota, U.S.A.
አድራሻችን: 4401 Minnehaha Avenue S., Minneapolis, MN 55406
ስልክ: (612) 721-1222
ኢሜይል: dsmachurch@gmail.com
ዌብሳይት: https://www.debreselam.net
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Debreselameotc/